About Course
ይህ የስልጠና ትምህርት የተዘጋጀው ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቃሚዎች በተለይም ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣
የገጠሩን ማህበረሰብ፣ እና ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሰዎችን በመሰረታዊ የዲጂታል አና የፋይናንስ እውቀት
በማስታጠቅ በዘመኑ የዲጂታል ዓለም ውስጥ ተሳትፏቸን ለመጨመር እና አዳዲስ የፋይናንስ
ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ለማስቻል ነው። በዘመነ ቴክኖሎጂ፤ ግንኙነቶች፣ ትምህርቶች፣ እና
የኢኮኖሚ እድሎች ሁሉ ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ባሉበት ጊዜ፤ በዘርፉ መሰረታዊ እውቀትን ማዳበር እጅግ
አስፈላጊ ነው።
ይህ ትምህርት በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ተደራጅቷል፡
ሀ. መሰረታዊ የዲጂታል እውቀት
ይህ ክፍል ተጠቃሚዎች ሞባይሎቻቸውን እና ኢንተርኔትን አእንዴት እንደሚጠቀሙ ማሳወቅ ላይ
ያተኩራል።
- የሞባይል ስልክ መተግበሪያዎችን መጠቀም፡ ይህ መሰረታዊ የሞባይል ስልክ አጠቃቀሞችን
(ስልክ መደወል፣ የጽሁፍ መልክት መላክ፣ አድራሻዎችን ማስተዳደር፣ እንደ ካልኩሌተር፣ እና
ባትሪን መጠቀም፣ አንዲሁም ዋትሳፕ፣ ቴሌግራም፣ እና ዩቲዩብን) መለየት እና መጠቀም ላይ
ያተኩራል። - መረጃዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት መፈለግ እና ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም፡
ተጠቃሚዎችን የቢዝነስ እና የግንኙነት ድህረ ገጾችን ማስተዋወቅ፣ በኢንተረኔት አጠቃቀም ላይ
ያሉ ጥንቃቄዎችን (የሚስጥር ቁጥር አጠባባቅ፣ እና ማጭበርበሮችን መለየት) ማስተማር እና
መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎቶችን ለምሳሌ ኢሜይል አጠቃቀም፣ መረጃ መፈለግ፣ እና
ዶክመንት አከፋፈትን ያሳያል።
ይህ ክፍል ለስራ ፈላጊዎች እና ጥቃቅን ቢዝነስ ለሚሰማሩ በዲጂታል አጠቃቀም በመብቃት ኮምፒውትረን
እና ኢንተርኔትን ለስራ መጠቀም እንዴት እንደሚቻል በማብራራት ይጠናቀቃል።
ለ. መሰረታዊ የፋይናንስ እውቀት
ይህ ክፍል ለተጠቃሚዎች መሰረታዊ የፋይናንስ ጽንሰ ሀሳቦችን በማንሳት የተሻለ የገንዘብ አያያዝንና ውሳኔ
አስጣጥን ያሳውቃል።
- በጀት ማውጣት እና የሂሳብ አያያዝ፡ ገቢን እና ወጪን መረዳትን፣ የቤት እና የቢዝነስ በጀት
አወጣጥን እና የሂሳብ አያያዝን ያስተምራል። - ቁጠባ፡ የቁጠባን ጥቅም፣ የቁጠባ አይነቶችን፣ (የአጭር ጊዜ፣ ለድንገተኛ ወጪ፣ አና ለረጅም ጊዜ)
እና ገንዘብን በጥንቃቄ ስለማስቀመጥ ይገልጻል። - ብድር፡ ለተጠቃሚዎች ስለ ብድር ጽንሰ ሀሳብ፣ የብድር ምንጮችን፣ እና አዋጪ የብድር
እውቀቶችን ለምሳሌ ስለ ወለድ እና የብድር ክፍያ ያስረዳል። - የፋይናንስ አገልግሎቶትች፡ የባንኮች፣ እና አነስተኛ የቁጠባ እና የብድር ተቋማትን አሰራር፤
የባንክን አካውንት ስለመክፈት እና ስለመጠቀም፣ እና ክፍያን ስለመፈጸም፣ ገንዘብ አላላክ፣ እና
ቁጠባ ያስረዳል። - ኢንሹራንስ እና የአደጋ ስጋት አስተዳደር፡ ኢንሹራንስ እንዴት ከፋይናንስ አደጋ እንደሚታደግ፣
ስለ ኢንሹራንስ አይነቶች (የጤና፣ የህይወት፣ የንብረት)፣ እና እንዴት ላልታሰበ ነገር (ድንገተኛ) ነገር
ማቀድ እንደሚያስፈልግ ያሳያል።
ሐ. መሰረታዊ የዲጂታል ፋይናን እውቀት፡
ይህ ክፍል ተጠቃሚዎች ኃላፊነት የሚሰማቸው እና በመረጃ የተደገፉ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያግዛል።
- የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች፡ እንደ የሞባይል ባንክ፣ ቴሌብር፣ ሄሎካሽ፣ ኤቲኤም፣
የሽያጭ ማሽን (POS) እና ዲጂታል ምንዛሬዎች ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ያስተዋውቃል። - የዲጂታል ብድር እና የብድር ነጥብ፡ በዲጂታል አውድ ውስጥ ብድር እንዴት እንደሚሰራ፣
የብድር ነጥቦች አስፈላጊነት፣ እና ከመጠን በላይ ዕዳ እና ማጭበርበሮችን እንዴት ማስወገድ
እንደሚቻል ያብራራል።
መ. የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ደህንነት እና ጥበቃ
የዲጂታል አጠቃቀም እያደገ ሲሄድ፣ ስጋቶችም እንዲሁ ይጨምራሉ። ይህ ክፍል ተጠቃሚዎች በዲጂታል
የፋይናንስ አገልግሎቶች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አስፈላጊ እውቀት ያስታጥቃቸዋል።
- የማጭበርበር መከላከያ፡ የኢሜል ማባበሎች (phishing)፣ ያጭር መልክት ማጭበርበር
(smishing)፣ የመደወል ማጭበርበር (vishing)፣ ሲምን መቀየር፣ እና የማንነት ስርቆት ያሉ
የተለመዱ ማጭበርበሮችን እና እነሱን እንዴት ለይቶ ማወቅ እና ማስወገድ እንደሚቻል ያሳያል። - የተጠቃሚዎች ጥበቃ፡ የተጠቃሚዎችን መብቶች እና ኃላፊነቶች፣ ማጭበርበርን እንዴት ሪፖርት
ማድረግ እንደሚቻል፣ እና ከፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በአስተማማኝ ሁኔታ እንዴት
መቀጠል እንደሚቻል ያስተምራል።
ይህ ኮርስ ተግባራዊ የዲጂታል ክህሎቶችን፣ መሰረታዊ የፋይናንስ እውቀትን እና የዲጂታል ደህንነት
ልምዶችን በማጣመር ተሳታፊዎች የዲጂታል መሳሪያዎችን በብቃት እንዲጠቀሙ፣ አገልግሎቶችን እና
እድሎችን እንዲያገኙ እና ለረጅም ጊዜ የሚሆኑ የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
በይዘቱም ቀላል፣ ለተጠቃሚ ምቹ በሆነ መንገድ የቀረበ ሲሆን ይህም ለሁሉም ተጠቃሚዎች፣ በተለይም
አነስተኛ የመደበኛ ትምህርት ወይም የዲጂታል ልምድ ላላቸው የተሻለ አማራጭ ያደርገዋል።

